ቅዱስ ያሬድ

የስሙ ትርጓሜ ያሬድ ማለት ርደት፣ ወሪድ፣ ማለትም መውረድ ማለት ነው፡፡ ከአዳም ስድስተኛ በሆነው በመላልኤል ልጅ በያሬድ ጊዜ ደቂቀ ሴት ከደብር ቅዱስ ወደ ደቂቀ ቃየን ወደ ምድረ ፍዳ ስለወረዱ ያንን ለማስታወስ አባቱ መላልኤል ያሬድ ብሎታል፡፡ “ወጸውዐ ስሞ ያሬድሃ እስመ በመዋዕሊሁ ወረዱ መላእክተ እግዚአብሔር ውስተ ምድር እለ ተሰይሙ ትጉሃነ፣ ስሙን ያሬድ ብሎ ጠራው በእርሱ ዘመን ትጉሃን ተብለው የሚጠሩ […]