Home / About Us
በደብረ ሐዊ የቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ሕንፃ ቤተክርስትያን፣ የልህቀት ማዕከል የሚሆንየአብነት ትምህርት ቤት እና ሙዚየም ፕሮጀክት ኮሚቴ፡-
በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በበየዳ ወረዳ በሳብራ ቀበሌ የሚገኘውን የቅዱስ ያሬድ አንድነትገዳም በዘመናዊ መንገድ ጥንታዊውን የአብነት ት/ቤት ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊትምህርት የያዘና ከሁለት ሺ በላይ ተማሪዎችን ሊያስተናግድ በሚችል መልኩ እንዲደራጅናየቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት የልቀት ማዕከል እንዲሆን እንዲሁም የጻድቁንሥራዎችንና ተጋድሎውን የሚያሳይ ቋሚ አውደ ርዕይ፣ዘመናዊ ሙዚየም እንዲገነባ እናዘመናዊ ቤተ ክርስቲያን በመሥራት ታሪኩን ጠብቆ ከመላው ኢትዮጵያ ለሚመጡትምምዕመናን በረከት የሚያገኙበት፣ ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ ጎብኚዎች የጉብኝት መዳረሻበማድረግ ሀገራችንም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝ የሚያስችል ፕሮጀክት በመንደፍ በአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትበመጀመሪያ በቁጥር 52/177/07 በቀን 11/02/07 ዓ.ም እና በቁጥር 4142/177/07 በቀን 01/11/2007 ዓ.ም ፈቃድ በማግኘቱ ተቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡