“ኢትዮጵያውያን ሆይ! እውነተኛውን ታሪክ ወደ መከተል እግራችሁንም ዐይናችሁንም አንሡ!”
አለቃ አያሌው ታምሩ
Become a Family    
International Payment    
ከሥር የተዘረዘሩትን የባንክ ቁጥሮች በመጫን ለደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ድጋፍ ያድርጉ።
ታሪካዊው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ጠፍ ሆኖ የነበረውን የገዳሙን አብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ ከሁለት ሺ በላይ ተማሪዎች ሊያስተናግድ በሚችል ሁኔታ ማደራጀትና ማስተማር እነዚህን ተማሪዎችና መምህራን የሚገለገሉበት ዘመኑ በደረሰበት የምህንድስና ጥበብ ደረጃውን የጠበቅ የልህቀት ማዕከል የሚሆን የአብነት ትምህርት ቤት፣ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ማሳነጽ እና የቅዱስ ያሬድን ሥራዎችና ተጋድሎ የሚገልጽ ቅርሶች በክብር የሚቀመጡበት ሙዚየም በመገንባት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች ታላቅ የሃይማኖትና የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግየሚያስችል ፕሮጀክት ነው፡፡
ታሪካዊው የደብረ ሃዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም የቤተ ክርስቲያኗን የአብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚያስተምር የልህቀት ማዕከል ማድረግና ምዕመናን ወደ ገዳሙ እየሔዱ በረከት የሚያገኙበት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች የቤተክርስቲያናችንንና የሀገራችን ቀደምትነት ገናና ባለታሪክ መሆናቸውን የሚረዱበትና ሀገራችንም የውጭ ምንዛሪ የምታገንበት ማድረግ.
ታሪካዊው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ የአንድነት ገዳም ጠፍ ሆኖ የነበረውን የገዳሙን አብነት ትምህርት ጥንታዊነቱን ጠብቆ ከሁለት ሺ በላይ ተማሪዎች ሊያስተናግድ በሚችል ሁኔታ ማደራጀትና ማስተማር እነዚህን ተማሪዎችና መምህራን የሚገለገሉበት ዘመኑ በደረሰበት የምህንድስና ጥበብ ደረጃውን የጠበቅ የልህቀት ማዕከል የሚሆን የአብነት ትምህርት ቤት፣ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ማሳነጽ እና የቅዱስ ያሬድን ሥራዎችና ተጋድሎ የሚገልጽ ቅርሶች በክብር የሚቀመጡበት ሙዚየም በመገንባት ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ጎብኚዎች ታላቅ የሃይማኖትና የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ
በአጠቃላይ ለሥራችን አመቺ ይሆን ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀራርቦ በመሥራት ለዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት በባለሙያ በቀረበው ጠቅላላ ጥናት መሰረት የወጪውን ዝርዝር ብር 4,000,000,000.00 (አራት ቢሊዮን ብር) እንደሚፈጅ የሚገመት ሲሆን የግንባታው ወጪ የሚሸፈነው በኢትዮጵያዊያን ልጆቿ በመሆኑ ዘር፣ ቀለም፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ሳይለየን በአንድነት በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያላችሁ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የዚህ ታላቅ ታሪካዊ ፕሮጀክት ባለቤት በመሆናችሁ በምትችሉት ሁሉ በገንዘባችሁ፣ በዕውቀታችሁ፣በጉልበታችሁ እና ከምንም በላይ በጸሎታችሁ ከጎናችን እንዳትለዩን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡